Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የ2013 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው፡፡
የግምገማ መድረኩም የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ በአባገዳ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ እንደተናገሩት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ብለዋል፡፡
በ6 ወራት የተሰሩ ስራዎች በህዝቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ተገምግሞ ተሞክሮ ይቀመራል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
በስራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች፣ ድክመቶችና ጥንካሬዎች ተለይተው ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣልም ነው ያሉት፡፡
በዚህ የግምገማ መድረክ የድርጅት፣ የፕሮጀክቶች፣ ሱፐርቪዥን እና ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የሴክተር መስሪያ ቤቶች የስራ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡
ብዙአለም ቤኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.