Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማእከልና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ማእከልና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት የመሰረት ድንጋይ በአምቦ ከተማ ተቀመጠ፡፡
የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአርቲስቱ 80 ቀን የሙት መታሰቢያ ላይ በመገኘት አስቀምጠዋል።
የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ይሄው መታሰቢያና ባህልና ታሪክ መዕከል አርቲስቱን ከማስታወስ ባለፈ መጭው ትውልድ ስለ ኦሮሞ ታሪክ የሚያውቅበት በርካታ ነገሮችን ያካትታል ተብሏል።
የመሰረት ድንጋዩን ባስቀመጡበት ወቅት አቶ ሽመልስ ባደረጉት ንግግር ማእከሉ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በብዙ መልኩ ለማስታወስ እና ለመጭው ትውልድ በበቂ መንገድ ለማስተማር ይጠቅማል፤ያስፈልጋል ብለዋል።
ሃጫሉ ቢያልፍም ሲታገልለት ለነበረው ነፃነትና እኩልነት መታገል ከሁሉም ይጠበቃል ፤ለዚህም የትኛውንም መስዋትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
የአርቲስቱን ጀግንነት ሁሉም በተምሳሌትነት በማየት ለበለጠ ድል መነሳት እንደሚገባ ነው የገለፁት፡፡
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.