Fana: At a Speed of Life!

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ ÷ “በኢትዮጵያዊ ልብ በህብረት ከሰራን፣ ለኑሮ ምቹ በሆኑ ከተሞች የተዋበችና የበለፀገች ኢትዮጵያን የምናይበት ዘመን ሩቅ አይሆንም” ብለዋል፡፡
ከተማና ከተሜነት በዕውቀትና በጥበብ ከተያዘ ፀጋ፣ በአግባቡ ካልተገራና በማስተዋል ካልተመራ ደግሞ አደጋ መሆኑን ጠቁመው ይህንን እውነታ በውል በመገንዘብ መንግስት ከምንጊዜውም በላይ ለከተሞች ዕድገትና መስፋፋት፣ ለዜጎች ህይወት ማማርና መቃናት የሚበጁ ስልቶችን በመንደፍ በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በ2013 በጀት ዓመት በትብበር ስለሰራን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ባልተመለሱ የልማት ጥያቄዎች ሲወዛገቡ ዓመታትን ላስቆጠሩ ከተሞቻችን ምላሽ መስጠት እንደምንችል በተግባር ያስመሰከርንበት ዓመት ነበር ሲሉም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም ኢንጅነር አይሻ መሃመድ ÷ የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ለማሳወቅ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ለነጩ ቤተመንግስት መርሃ-ግብርን አስጀምረዋል፡፡
መድረኩ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በ2013 በጀት አመት በዘርፉ የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ቀርበው ሰፊ ውይይት እንደሚደረግባቸው ከከተማና ልማት ኮንስትራክሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.