Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ወ/ሮ አዳነች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ከወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና አርቲስቶች ጋር ጃንሜዳን አፅድተዋል፡፡

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ገፃቸው እንዳስታወቁት ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ዝግጁ እንዲሆን የሚሰራው ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በዓሉ ድምቀቱን፣ እሴቱን እና ውበቱን በጠበቀ አግባብ እንዲከበርም እየሰራን ነው ብለዋል።

በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስም ጠቁመዋል፡፡

የአትክልት መገበያያ ስፍራዎችን በሌሎች አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ጎን ለጎን እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች ከነገ ጀምሮ ወደ ሀይሌ ጋርመንት ሙሉ በሙሉ ይሸጋገራሉም ነው ያሉት፡፡

ነጋዴዎች ወደ ጋርመንት በሚዘዋወሩበት ሁኔታዎች ዙሪያ ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎችን ተዘዋውረው አነጋግረዋል፡፡

በቦታው የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት የከተማ አስተደዳሩ ላደረገው ድጋፍ ሁሉ ምስጋና አቅርበው ከነገ ጀምሮ ከተማ አስተዳደሩ በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት በተዘጋጀው ቦታ ለመዘዋውር ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ስራው የጋራ ነው ብላችህ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ባለድርሻ አካላት ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁም ብለዋል ወይዘሮ አዳነች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.