Fana: At a Speed of Life!

የከተራ በዓል በምንጃር ኢራንቡቲ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ. ቢ.ሲ) የጥምቀት ከተራ በአል በኢራምቡቲ 44ቱ ታቦታት በአንድ ላይ ሆነው በድምቀት ተከበረ ።
በዓሉ ሲከበር 620 ዓመታትን አስቆጥሯል ያሉት የምጃር ሸንኮራ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ዋልተንጉስ ዘርጋው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ጥምቀት በኢራቡቲ ወንዙ አምሳለ ዮርዳኖስ በመሆኑ ከላይ መነሻው አንድ ኾኖ መሐል ላይ ለሁለት ተከፍሎ ዝቅ ብሎ መገናኘቱ አምሣለ ዮርዳኖስ አሰኝቶታል ብለዋል፡፡
ውኃው ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ መፍሰሱና ከመነሻው ጀምሮ የ44ቱም ታቦታት ጸበል መኖሩ እንዲሁም ወንዙ ተፈጥሯአዊ በመሆኑ እና 44 ታቦታት በአንድ ላይ ማደራቸው በተለይም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጽላት አብሮ በጥምቀተ ባህር ማደሩ የተለየ ያደርገዋል ነው ያሉት።
የበዓል አከባበሩ አሁን ላይ በሀገራችን እየታወቀ ከአካባቢው ነዋሪዎች ባለፈ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቦታው ድረስ እየመጡ ማክበር ጀምረዋል ያሉት ሀላፊው፥ በቀጣይም ይበልጥ የማስተዋወቅ ስራ በመስራት በዓሉ በተለየ መንገድ እንዲከበር እሰራለን ነው ያሉት ።
በዓሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቃና ዘገሊላ በድምቀት እንደሚከበር ነው ከወረዳው ባህልናቱሪዝም ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
በአበበ የሸዋልዑል
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.