Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ፣ መቅደላ ዓምባ እና የወቻሞ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቀዋል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም ዩኒቨርሲቲው 2 ሺህ 182 ተማሪዎችን ለ7ኛ ጊዜ ማስመረቁን ጠቁመው ከተመራቂዎቹ መካከል በመደበኛ መርሃ-ግብር ውስጥ 1 ሺህ 636 ተማሪዎች፣ በቅዳሜ እሁድ 401 ተማሪዎች፣ 145 ተማሪዎች ደግሞ የድህረ-ምረቃ ምሩቃን መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 33 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ዶክተር ከማል አመልክተዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርስቲው ቦርድ ሰብሳቢ እና የትራንስፖርት ሚንስትር ዴኤታ አቶ አወል ወግሪስ፣ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ዕውቀት አግኝተው የተመረቁ ተማሪዎች ሀገሪቱን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለማላቀቅ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ኃላፊነት ይዘው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ተመራቂዎች ያገኙትን ክህሎት በመጠቀም ከስሜታዊነትና በጸዳ መልኩ አሁን ላለው ሀገራዊ ሁኔታ የመፍትሔ አካል መሆን እንደሚጠበቅባቸውም አቶ አወል ማሳሰባቸውን ከቤኒሻንጉን ኩሙዝ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የመቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው ዕለት በመካነሰላም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢው 344 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 137ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡
ዩኒቨርስቲው በትናትናው ዕለትም በተፈጥሮ ሳይንስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 480 ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይም የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ዱራሜ ካምስ በመጀመሪያ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 257 አስመርቋል።
የወቻሞ ዩኒቨርስቲ ኘሬዚዱንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ÷ የኮሮና ወርሽኝ ፈተና በሆነበት ጊዜ የተመረቁ ተማሪዎች ማህበረሰቡን የሚገጥሙ ማናቸውንም ችግር በእውቀት ለመፍታት መስራት አለባቸው ብለዋል።
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ተማሪዎች ከነበረባችሁና ካለፋችሁት ሀላፊነት በላይ የወደፊቱ የቤት ስራ ብዙ መሆኑን አዉቃቹ መዘጋጀት አለባችሁ ብለዋል።
ሀገር የሚገነባው በናንተ መሆኑንና የወደፊት የኢትዮጵያ እጣፋንታ በናንተ እጅ መሆኑን መረዳትና ለዛም በቂ ዝግጅት ልታደርጉ ይገባል ብለዋል።
በጥላሁን ይልማ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.