Fana: At a Speed of Life!

የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ፕሬዚዳንቱ ረቡዕ ዕለት ከሞሮኮ ወደ ካይሮ ከተመለሱ በኋላ ቀለል ያለ የሳል ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገላቸው ምርመራ በዛሬው ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል።
በመሆኑም ፕሬዚዳንቱ ቢያንስ ለቀጣዮቹ 14 ቀናት በሆቴላቸው ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
እንዲሁም ባለፉት ሰባት ቀናት በተለይ በሞሮኮ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያሳውቁ እና አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ተጠይቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.