Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በስድስት ወራት 9ነጥብ 46ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በስድስት ወራት 9ነጥብ 46ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

ቢሮው የ2013 የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ10ዓመት እቅድ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ትውውቅ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የገቢዎች ቢሮ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ፡፡

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን በ2013 በጀት ዓመት 20ነጥብ 56ቢሊየን ብር እንዲሁም በስድስት ወራት 10ነጥብ 7ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በስድስት ወራት ውስጥ 9ነጥብ 46 ቢሊየን ብር መሠብሰብ መቻሉን ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በአፈፃፀሙ የበጀት አመቱን 46ነጥብ 5 በመቶ መሰብሰበ የተቻለ ሲሆን ከስድስት ወራቱ ደግሞ 93 በመቶ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ይህም ካለፈው አመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 2ነጥብ 8ቢሊየን ብር ወይም 44 በመቶ ብልጫ መኖሩን ነው ሀላፊዋ የገለፁት፡፡

የተመዘገበው ውጤት ከአሁን እና ካለፈው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ጥሩ ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጅ የስድስት ወራት ዕቅድ 93 መቶ በመሆኑ የበጀት አመቱን መቶ በመቶ ለመፈጸም አሁንም በትኩረት መስራት አለብን ብለዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.