Fana: At a Speed of Life!

የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰዉ ዝርፊያ የሚፈጽሙ እንዳሉ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰዉ፣ሀሰተኛ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘዉ ህገ-ወጥ ብርበራና የዝርፊያ ሙከራ የሚፈጽሙ እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው ማሳሰቢያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተሰጠ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ህግ የማስከበር ተግባር እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።

ሆኖም የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ ፖሊስ ወይም የፀጥታ አካላት ነን በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንፁሃን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያስፈራሩ ግለሰቦች እንዳሉ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የፌደራል፣ የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰዉ፣ሀሰተኛ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘዉ ህገ-ወጥ ብርበራና የዝርፊያ ሙከራ የሚፈጽሙ እንዳሉ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃዎችንም አሰባስቧል፡፡

በመሆኑም እንደነዚህ ዓይነት መሰል ድርጊት የተፈፀመባችሁ ግለሰቦች ወይም በቀጣይ ተመሳሳይ ሁኔታ ከህግና አሰራር ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥማችሁ ድርጊቱ ህገ-ወጥ ስለሆነና በአሸባሪው ህወሃት ጁንታ ቡድን ርዝራዦች ሊፈፀም ስለሚችል ይህንን አውቃችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የተቋሙ የስልክ መስመሮች ፈጥናችሁ በመደወል ህገ-ወጥ ግለሰቦችን ለህግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ለሚደረገው ጥረት የበኩላቹን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያስታውቃል፡፡

ነፃ የስልክ መስመሮች 987፣ 816 እና 991, (አዲስ አበባ ፖሊስ)
ለወንጀል መከላከል ስልክ ቁጥር 0115524077
ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የቢሮ ስልክ ቁጥሮች 0115309027 ፣0115309231 እና 0115309077
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቢሮ ስልክ ቁጥር 0111110111 ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.