Fana: At a Speed of Life!

የክርስቲያል አውቶሞቲቭ ድርጅት የኮቪድ-19 ተጠርጣሪዎችን እና ህሙማንን ለሚያመላልሱ አምቡላንሶች ነፃ የኬሚካል ርጭትና እጥበት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የክርስቲያል አውቶሞቲቭ ድርጅት የኮቪድ-19 ተጠርጣሪዎችን እና ህሙማንን ለሚያመላልሱ አምቡላንሶች ነፃ የኬሚካል ርጭትና እጥበት አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በስምምነቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ በርካታ ግለሰቦችና ተቋማት ለሀገራዊ ጥሪው ምላሽ እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የክርስቲያል አውቶሞቲቭ ተግባርም የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በኩል ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የክርስቲያል አውቶሞቲቭ ድርጅት ማኔጅንግ ዳሬክተር አቶ ዳዊት ውብሸት በበኩላቸው የአንቡላንሶች ደህንነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ነፃ የኬሚካል ርጭትና እጥበት አገልግሎት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.