Fana: At a Speed of Life!

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ የመከላከያ ሠራዊትን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ‹‹የሀገር ጥሪን ስቀበል ለመጪው ትውልድ ፍቅርን አስተምራለሁ›› በሚል የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ ጌጢቱ ሲሳይ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ተቀላቅለዋል፡፡
አፈ-ጉባኤዋ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ላባደር ክፍለ ጦር ኮምቦልቻ ብርጌድ ከተራ ተዋጊ እስከ ውጊያ ኦፕሬተር እንዲሁም እስከ 1992ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትየስራ ድርሻዎች አገልግለዋል፡፡
በነገው እለት ወደ ውጊያ ግንባር ጉዞ ለማድረግ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
«ጁንታው እኛ እያለን ሀገር ለማፈራርስ ማሰቡ ትክክል ባለመሆኑና ልጆቼን ማሳደግ የምችለው ሀገር ሰላም ስትሆን በመሆኑ የሀገርን ጥሪ ተቀብያለሁ›› ያሉት አፈ-ጉባኤዋ ‹‹የሀገር ጥሪን ስቀበል ለመጪው ትውልድ ፍቅርን አስተምራለሁ›› ብለዋል፡፡
ለሀገራችን አንድነት ሁላችንም የተቀጣጠለውን የመከፋፈል እሳት ማጥፋት አለብን ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
የፅህፈት ቤቱ ባለሞያዎች የሀገራን ጥሪ ተቀብለዋል ወደ ውጊያ ግንባር ስለሚሄዱ የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ በመስጠት ሽኝት አድርገዋል ሲል የአዲስ አበባ ብልጽግና አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.