Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ባለ 5 እና 4 ኮኮብ ሆቴል ኢንቨስተመንት የቦታ ርክክብ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ባለ 5 እና 4 ኮኮብ ሆቴል ኢንቨስተመንት የቦታ ርክክብ አካሂዷል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ከማል መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ የሆቴል ኢንቨስትመንቶቹ በጠቅላላው በ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የሚካሄዱ ናቸው።

በከተማዋ በሚከናወነው የስድስት ሆቴሎች ኢንቨስትመንትም ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጠርም አስታውቅዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ በኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተመራጭ እና እያደገ የመጣ ነው ያሉት ዶክተርር ከማል፥ የቱሪዝምና ጠቅላላ የአገልግሎት ዘርፉ አቅርቦቱን የሚሸከም እንዲሆን 5 ባለ 4 ኮኮብ ሆቴሎች መገንባት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ እስከ ሶስት አመት ውስጥ ባለው ጊዜ የሚጠናቀቁ መሆናቸውንም የኮምቦልቻ ከተማዋ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ከማል መሀመድ ጨምረው ገልፀዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.