Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ክትትል የሚያደርግ ብሄራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ክትትል የሚያደርግ ብሄራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ተቋቋመ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በምክር ቤቱ ካለፉ ውሳኔዎች መካከልም በጤና ሚኒስቴር የሚመራ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ክትትል የሚያደርግ ብሄራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ማቋቋም ነው።

በዚህም የሚከተሉትን አባላት ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁመዋል÷

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል – የሰላም ሚኒስትር

አቶ አህመድ ሽዴ- የገንዘብ ሚኒስትር

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ- የገቢዎች ሚኒስትር

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው -የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ – የትራንስፖርት ሚኒስትር

ዶክተር ሊያ ታደሰ- የጤና  ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.