Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ምልክት ያልታየባቸው 2 ሺህ 90 ሰዎች ክትትላቸው እንዲረቋጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው የኮሮና ቫይረስ ምልክት ያልታየባቸው 2 ሺህ 90 ሰዎች ክትትላቸው እንዲረቋጥ መደረጉን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ከውጭ ወደ ሀገር የገቡ 636 መንገደኞች ተለይቶ እንዲቆይ በተወሰነው መሰረት እስካሁን ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።

መንገደኞቹ ባሉባቸው ሁሉም ሆቴሎች የጤና ባለሙያዎችን በመመደብ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

በሌላ በኩል ከላይ የተገለፀው ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገር የገቡ 873 ሰዎች በቤታቸው ሆነው በስልክ ለ14 ቀን በጤና ባለሙያዎች የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳዩ ሰባ ዘጠኝ (79) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸውና የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ከሚገኙ ታማሚዎች ውስጥ አንድ (1) ታማሚ በድጋሚ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ መሆናቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት ተጨማሪ የህክምና ክትትል እየተደረገው እንደሚቆዩ ተገልጿል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.