Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ እናቶችን ልጆቻቸውን ጡት ከማጥባት እንደማያግዳቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እናቶችን ልጆቻቸውን ጡት ከማጥባት እንደማያግዳቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

28ኛው ዓለም ዓቀፍ ጡት የማጥባት ቀን ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ”ለአገር ጤና ጡት ማጥባትን እንደግፍ” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።

በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ያዘጋጀው የጤና ሚኒስቴር በዓሉ በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጊዜ እንደሚከበር አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የእናቶችና ሕፃናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም አንዳንድ እናቶች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ሳቢያ ለልጆቻቸው የቆርቆሮ ወተት እያጠጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ነገር ግን እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት እናቶች ልጆቻቸውን እንዳያጠቡ የሚል ጥናት አልተካሄደም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.