Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ፖለቲካዊ ማድረግ መቆም አለበት-የዓለም የጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ፖለቲካዊ ማድረግ መቆም አለበት ሲሉ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን የገለጹት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ወረርሽን ምክንያት በማድረግ የዓለም ጤና ድርጅት ላይ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ነው።

ፕሬዚዳንቱ በአስተያየታቸው የዓለም ጤና ድርጅት አሰራር ለቻይና የወገነ እና ለወረርሽኙ ምላሽ ለመስጠት የዘገየ ነው ብለውታል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ቴድሮስ የፕሬዚዳንቱን ክስ ውድቅ አድርገው  “የኮቪድ-19ኝ ወረርሽኝን ፖለቲካዊ ማድረግ አይጠቅምም፤ ሊቆም ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት ከዘርና ቀለም በጸዳ ሁኔታ ለሁሉም ህዝብ ቅርብ ሆኖ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት ዶክተር ቴድሮስ።

ሃላፊው አያይዘውም አሁን የሚያስፈልገው ሁሉም በአንድነት ሆኖ ወረርሽኙን ለመከላከል በጋራ መስራት ነው ብለዋል።

የአሜሪካ መንግስት የዓለም የጤና ድርጅት አመራሮች ላይ የጀመረውን ዘመቻ ተከትሎ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ከዶክተር ቴድሮስ ጎን መቆማቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.