Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ 19 መመሪያን በማይተገብሩ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን ገቢራዊ የማያደርጉ ተቋማትና ግለሰቦችን በህግ የመጠየቁ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል ጤና ቢሮዎች አስታወቁ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የድንገተኛ አደጋ ቁጥጥር እና የጤና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ገመቹ  ሹሜ  እንደገለጹት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ የሚስተዋለው የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ በየዕለቱ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ለቫይረሱ ተጋልጠው ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ እና ለህልፈት የሚዳረጉ ዜጎች ቁጥርም እጅግ አሰሳቢ ደረጃ ደርሷል ነው ያሉት፡፡

በአንጻሩ የዜጎች መዘናጋት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ያሉት አቶ ገመቹ፣ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የደቡብ ክልል የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው፣ በክልሉ የወረርሽኙ ስርጭት ምጣኔ ከፍተኛ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አብዛኞቹ በእድሜ የገፉ እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ከመሆናቸው ጋር ተያይዞም  ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ታማሚዎች መበራከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ስለ ኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች በማስተማር  ብቻ የባህሪ ለውጥ ማምጣት አልተቻለም ያሉት ሃላፊዎቹ፣ በቀጣይ መከላከያ መንገዶችን ገቢራዊ የማያደርጉ  ግለሰቦች  እና  ተቋማትን  በህግ የመጠየቁ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.