Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያግዙ የሕክምና ቁሳቁሶች ለጤና ሚኒስቴር ተበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያግዙ የሕክምና ቁሳቁሶች ከተለያዩ ተቋማት እና በውጭ ሃገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተበረከተለት፡፡

የተበረከቱት ድጋፎች የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብል፣ የሕክምና አልባሳት፣ የንጽሕና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮች እና የሙቀት መለኪያዎች ይገኙበታል፡፡
በዚህም ላየን ክለብ ኢንተርናሽናል 500 መቶ ሺህ ብር የሚገመቱ በሀገር ውስጥ የተመረቱ የሕክምና አልባሳት፣ በፍራንክፈርት ቆንስላ ጀነራል የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት እና የኢትዮጵያ ወዳጆች 82 ሺህ 247 ዩሮ ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁሶች እና አልባሳት፣

በቻይና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኮሚዩኒቲ 20 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው 50 የታማሚዎች መከታተያ መሣሪያዎች እንዲሁም ዳይሬክት ኤድ እና ጉዳ ጉያ ቴክስታይል ማኑፋክቸሪንግ የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መሰል ድጋፎች ሚኒስቴሩ የተለያዩ አካላትንና ባለሙያዎችን በማስተባበር ድጋፍ ለማሰባሰብ እያደረገ ላለው ጥረት እገዛቸው ላቅ ያለ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ድጋፎቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ህብረተሰቡም የጥንቃቄ ምክሮችን ተግባራዊ እንዲያደርግ እና ራሱን ከኮቪድ19 እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.