Fana: At a Speed of Life!

የኳታሩ ስሀይል የብረት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኳታሩ ስሀይል የብረት ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

ኳታር የሚገኙት የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዛሬው እለት የኩባንያውን የብረታ ብረት እና የባትሪ ማምረቻ ፋብሪካዎች መጎብኘታቸውን በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ከጉብኝቱ በኋላም የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከስሀይል የብረት ፋብሪካ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዛይድ አቦካሎውብ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ኩባንያው በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ የጠየቁ ሲሆን፥ መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዛይድ አቦካሎውብ በበኩላቸው፥ ኩባንያው ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ለሁለት ጊዜያት የቅድመ ኢንቨስትመንት ዳሰሳ ማድረጉን አስታውቀዋል።

“ሁለተኛ ቤታችን በሆነችው ኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት አለን፤ ለዚህም ዝግጁ ነን” ሲሉም ስራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

ኩባንያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ፋብሪካውን ቢትዮጵያ ለማቋቋም እንደሚሰራ እና በመጀመሪያ ምእራፍም በአውሮፓ መስፈርት ኮፐር፣ አሉሙኒየም እና ዚንክ ማነቀባበሪያዎችን እንዲሁም አገለግሎት የሰጡ ባትሪዎችን ዳግም መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ፋብሪካዎችን ስራ እንደሚያስጀምር አስታውቀዋል።

በሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ ባትሪዎችን በማም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.