Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመርቋል፡፡

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ካምፓስ የሆነዉ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣የሚኒስቴር መስሪቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የደቡብ ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች የክልል የተለያዩ አመራሮች፣የወላይታ እና ዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አመራሮችና የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች አቅም በፈቀደ መልኩ ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ በፍተሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ትምህርት፣ምርምር እና ሳይንሳዊ ባህሎችን እያጎለበትን መሄድ ሀገራችን ለምታደርገዉ የዕድገትና የብልጽግና ጉዞ የማይተካ ሚና ስላላቸዉ ዩኒቨርስቲዎቻችን ይህንኑ በዉል በመገንዘብ በትጋት መተግበር አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለፍትሐዊነትና ተደራሽነት የትምህርት ተቋማትን በምናስፋፋበት ወቅት ተቋሞቻችን ለትምህርት ጥራትም ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሩ ማንሳታቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.