Fana: At a Speed of Life!

የወሎና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቀዋል።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ 429 የድኅረ ምረቃ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ በመታገዝ ነው ተማሪዎቹን ያስመረቀው።

ዛሬ የተመረቁት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች 359 ወንድ እና 70 ሴት፤ በድምሩ 429 መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አባተ ጌታሁን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች በድኅረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 72 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በኢንተርኔት አገልግሎት አማካኝነት በዙም ቴክኖሎጂ ታግዞ ያሰለጠናቸውን 72 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ አስመርቋል።

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው፥ ተመራቂ ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ በኢንተርኔት በመታገዝ ከመምህሮቻቸውና ከምርምር አማካሪዎቻቸው ጋር እየተገናኙ ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

ተመራቂ ተማሪዎችም፥ ቀጣይ በምርምር ሥራ እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.