Fana: At a Speed of Life!

የወምበራ ወረዳ ማህበረሰብ ለሰራዊቱ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን የወምበራ ወረዳ ማህበረሰብ በግንባር ለሚገኙ የሰራዊት አባላት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉጌታ አዲሱ እንደተናገሩት÷ የወረዳው ህዝብ ሰራዊቱን ለመደገፍ በ560 ሺህ ብር ወጪ 15 በሬ ፣ 13 ፍየል ፣ 4 በግ እንዲሁም 10 ኩንታል እህል አዘጋጅተው አስረክበዋል ::

በአካባቢው የሚገኝ ሻለቃ ዘመቻ ሃላፊ ሻምበል ዘውዱ ቱራ ÷ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ ለሰራዊቱ የበለጠ ሞራልና ወኔን የሚቀሰቅስ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.