Fana: At a Speed of Life!

የወራቤ ዩኒቨርስቲ ለወልድያ ዩኒቨርስቲ ከ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰበት የወልዲያ ዩኒቨርሲቲን ስራ ለማስጀመር የሚሆን ከ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው ካደረጋቸው ድጋፎች መካከል ኮምፒዩተሮች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ፈርኒቸሮች እንዲሁም ለተማሪዎች መማሪያና መመገቢያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ይጠቀሳሉ ።

የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑ ተገልጿል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ተወካይ አቶ ከድር ሽፋ ፥ ድጋፉ ዩኒቨርስቲው ወደ መደበኛው የመማር ማስተማሩ ሂደት በቅርቡ እንዲመለስ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲን በሙሉ አቅሙ ስራ ለማስጀመር ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር አበበ ግርማ ፥ ለድጋፉ ምስጋና ማቅረባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.