Fana: At a Speed of Life!

የወንጀል ስነ- ስርዓትና የማስረጃ ረቂቅ ህግ የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተሻለ ሁኔታ ለማስከበር ያስችላል- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወንጀል ስነ-ስርዓትና የማስረጃ ረቂቅ ህግ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ተወያይቷል።
በውይይቱ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደተናገሩት ሥራ ላይ የነበረው ህግ ከምርመራና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲፈጸሙ በር ከፍቷል።
በዚህም ሳቢያ ጥናቶችን በማካሄድና አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር ረቂቅ ህጉ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ረቂቅ ህጉ የተጠርጣሪዎችንም ሆነ የወንጀል ተጎጂዎች መብት አስመልክቶ የሚቀርቡ ስሞታዎችንና ቅሬታዎችን ለመፍታት ያስችላል ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ የዜጎችን መብት እንደሚያስከብርም ተናግረዋል።
ረቂቁ ህጉ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ከአገሪቱ ህገ -መንግስትና አገሪቱ ከተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመና የወንጀል ፍትህ አሰራርን እንደሚያዘምን ነው ያስረዱት።
ካሁን በፊት የነበረው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ እየዘመነ ከመጣው የወንጀል አፈፃፀም ስልት ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ የህግ ማእቀፉን ወደ ዘመነ አሰራር ለማሸጋገር ሁነኛ መፍትሄ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በረቂቅ ህጉ ላይ ጥናቶችን በማካሄድና አለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በመመልከት አዲስ የወንጀለኛ ህግ መመረቀቁን ዶክተር ጢሞቲዎስ አስታውቀዋል፡፡
የተሻሻለው ረቂቅ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ከሀገሪቱ ህገ መንግስት እንዲሁም አገሪቱ ከተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመና የወንጀል ፍትህ አሰራሩን እንደሚያዘም ነው አስረድተዋል።
የምክር ቤቱ የህግ፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አቡ ብርኪ በበኩላቸው በረቂቅ ሕጉ ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት እንደተሰባሰበ ገልጸው÷ በቅርቡም ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።
ረቂቅ ህጉ ግልፅ፣ በቀላሉ መረዳት የሚቻል፣ ከሌሎች ሕጎች ጋርበማገናዘብ መዘጋጀቱን አመልክተው ለአገር ሰላምና አንድነት ምሰሶ የሆነውን የህግ የበላይነት ለማስከበርም የተሻሻለው ረቂቅ ህግ ድርሻ እንደሚያበረክት መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.