Fana: At a Speed of Life!

የዋን ወሽ ምዕራፍ 2 መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋን ወሽ ምዕራፍ 2 መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

መርሃ ግብሩ 309 የገጠር ወረዳዎች እና 69 አነስተኛ እና መካከለኛ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

ፕሮግራሙ በንፁህ ውሃ አቅርቦት እና በመፀዳጃ ግንባታ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚተገበር ይሆናል።

በተለይም በገጠራማ የሃገሪቱ አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የጤና እና ማህበራዊ ችግሮችን የሚያቃልል መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና፣ የትምህርት እና የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሮች እንደገለፁት፥ ፕሮግራሙ የህብረተሰቡን የንፁህ መጠን ውሃ ፍላጎት እና ከውሃ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ይቀርፋል።

ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያም 569 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተመደበ ሲሆን፥ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

 

በመለሰ ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.