Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ሃይሎች ለኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት መሻከር ምክንያት ሆነዋል- ሱዳናዊያን የፖለቲካ ተንታኞች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ሃይሎች በሱዳን ውስጣዊ ጉዳዮች የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ለኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት መሻከር ምክንያት መሆኑን የሱዳን ፖለቲካ ተንታኞች ተናገሩ።
ኢትዮጵያና ሱዳን ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ሲሆኑ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግንኙነታቸው እየሻከረ መጥቷል ተብሏል፡፡
የወቅቱ የሱዳን መንግስት በተለይም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ደህንነት ላይ ከንቱና ያልተረጋገጡ ሰበቦችን በመደርደር የሶስትዮሸ ድርድሩን ማስተጓጎሉን መቀጠሉም ተገልጿል፡፡
የሱዳን መንግስት በሁለቱ አገራት የድንበር አለመግባባቶቸን ለመፍታት የተቋቋመውን የጋራ የድንበር ኮሚሽኖች ወደ ጎን በመተውና የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር በሃይል ጥሶ በመግባት ወረራ ፈጽሟል።
ይህም የሁለቱ አገራት የቆዬ መልካም ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለመሻከሩ በበምንያነት ይጠቀሳል ነው የተባለው፡፡
ሱዳናዊያን የፖለቲካ ተንታኞች ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የውጭ ሃይሎች በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ላይ እያደረጉ ያሉት ጣልቃ-ገብነት ለሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ግንኙንት መሻከር በምክንያትነት አንስተዋል።
የፖለቲካ ተንታኙ ሐሊ ያህያ በርካታ የውጭ ሃይሎች በአፍሪካ ቀንድ የሚያልሙትን ግላዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር በሱዳን ውስጣዊ ጉዳይ ገብተው እየፈተፈቱ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁሉን አሸናፊ በሚያደርግና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ድርድር እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረቧንም አስታውሰዋል።
ምንም እንኳ በርካታ የሱዳን ምሁራንና ፖለቲከኞች የግድቡ ግንባታ ለሱዳን ህዝብ አውንታዊ ሚና እንደሚኖረው ቢመሰክሩም÷ ዳሩ ግን የሱዳን መንግስት በተቃራኒው በአፍራሽ ተግባራት ላይ ተጠምዷል ብለዋል።
በኢትዮ-ሱዳን መካከል የተፈጠረው የድንበር ውዝግብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፈታት እንደሚቻልም ነው ያነሱት።
የውጭ ኃይሎች ግን የጋራ የጥቅምና ትስስር ያላቸውን ኢትዮጵያና ሱዳንን በሚጎዳ መልኩ ጉዳዩ በኅይል እንዲፈታ እንደሚሹ ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.