Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ላይ ተፈጥሮ በነረው ክስተት በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሃዘን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሃሙስ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ላይ ተፈጥሮ በነበረው ክስተት በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሃዘን ገለፀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ/ም በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተው ግጭት የተሰማውን ሃዘን ገልፆ በአደጋው ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

እንዲሁም ሚኒስቴሩ ሁለቱ አገራት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ እና በጋራ ለማጣራት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በአጎራባች የአካባቢ እና የክልል አስተዳደሮች መካከል የተቀናጀ ትብብር ቀጣይነት እንዲኖረው ጥሪውን አስተላልፏል ፡፡

ችግሮቹ በተሻለ ሁኔታ መፍትሔ የሚያገኙት በሁለቱ አገራት መካከል ባለው መልካም፣ ወዳጃዊ እና ሰላማዊ ግንኙነት ላይ በመመርኮዝ ነው ብሏል በመግለጫው ፡፡

ይህ ክስተት በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት እንደማይወክልም እናምናለን ነው ያለው ሚኒስቴሩ ፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል መልካም ግንኙነትን እና መግባባትን መሠረት ያደረገ የረጅም ጊዜ ግንኙነቶችን የሚያንፀባርቅ ጠንካራና ወዳጃዊ ካባቢን የበለጠ ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.