Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሌይ ጋር ተወያዩ።

አቶ ገዱ የዓለም ምግብ ድርጅት ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤ ኢትዮጵያ ከፕሮግራሙ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ያለበትን ደረጃ እና ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመግታት እያከናወነች ያለውን ስራ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

የበረሃ አንበጣና የጎርፍ አደጋ በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሃገራት እያደረሰ ያለውን ጉዳት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከምንጊዜውም በላይ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ድጋፍ በእጅጉ እንደሚፈልግና የዓለም የምግብ ፕሮግራም እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተሻለ አጠናከሮ እንዲቀጥል አቶ ገዱ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ገዱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሶስቱ አገሮች ያላቸውን ልዩነት በውይይትና በድርድር እንዲፈቱ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሌይ በበኩላቸው ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን፣ የበረሃ አንበጣንና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴም አድንቀዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለም ስጋት በመሆኑ የሁሉም አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን ዴቪድ ቤስሊይ ጠቁመዋል።

ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ሶስቱ አገሮች ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት አለባቸው ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.