Fana: At a Speed of Life!

የዓለምን የዋጋ ግሽበት እያባሰው ያለው የቡድን 7 ሀገራት በሩሲያ ላይ የሚጥሉት ማዕቀብ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በጀርመን የተሰበሰቡት የቡድን 7 ሀገራት በሩሲያ ላይ አዲስ ተጨማሪ አዲስ ማዕቀብ ጥለዋል።

የዩክሬን ቀውስን ተከትሎ እየተጣሉ ያሉት ማዕቀቦች ወደ ሩሲያ ኢኮኖሚ ምንም ዓይነት የውጭ ካፒታል እንዳይገባ ለመገደብ የተነደፉ መሆናቸውም ይነገራል።

አሁን ይፋ ያረጓቸው ማዕቀቦች መካከል የሩሲያን የወርቅ ምርት ኢላማ ያደረገ ነው። ሲጂቲኤን በድረገፁ ያወጣው የዓለም ፖለቲካ ተመራማሪው ፍሬዲ ሬዲን ፅሁፍ “ይህ አዲስ ማዕቀብ ለውጥ ያመጣ ይሆን?” ሲል ይጠይቃሉ።

ፀሃፈው በምዕራባውያኑ ሀገራት የተጣሉት ማዕቀቦች የዓለምን የዋጋ ግሽበት በማማባስ ራሳቸውን ማእቀብ የጣሉ ሀገራትን ሳይቀር በአስከፊ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ እንደከተታቸው ያስረዳል።

የጀርመኑ መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ የተጣሉት ማዕቀቦች እንዲነኩ ከሚታሰቡት ሀገራት ይልቅ ማእቀብ በጣሉት ሀገራት ላይ ያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ የበለጠ ሊሆን አይግባም ሲሉ ተደምጠዋል።

የቡድን ሰባት ሀገራት እና የአውሮፓ ህብረት አባላት የሩስያ ወርቅ ግዢን በመጋቢት ወር አቁመዋል።

በመሆኑም የወርቅ ዋጋ ወደ 1 ሺህ 856.86 የአሜሪካ ዶላር በማሻቀብ የዋጋ ግሽበትን አስከትሏል።

በፈረንጆቹ 2021 የሩሲያ የወርቅ ወጪ ንግድ ከ15 ቢሊየን ዶላር በላይ ደርሷል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፥ ነገር ግን የሀገሪቱ የወርቅ ምርት ሽያጭ ከሰኞው ማዕቀብ በፊት አሽቆልቁሎ እንደነበር ያትታሉ።

የአሁኑ የቡድን 7 አገራቱ አዲስ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ለያዙት አቋም ተምሳሌታዊ መልክ ከመስጠት ያለፈ ሌላ ትርጉም የለውም ባይ ናቸው።

እጅጉን በኢኮኖሚ ተሳስራ በምትኖረው ዓለም በሩሲያ ላይ እየተጣሉ ያሉት ማእቀቦች ሁለቱንም ወገኖች ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ያስርዳሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ላይ በጣለቻቸው ማእቀቦች ምክንያት በሀገሯ የከፋ የኑሮ ውድነትን እንድታስተናግድ አድርጓታል።

ዩክሬን በፊናዋ ይህ የኢኮኖሚ ማዕቀቦች ፈጣን ለውጥ አምጥተው ከገጠማት ጦርነት በፍጥነት እንድትወጣ እንደማያደርጋት በመገንዘብ ምዕራባውያኑን እየተማፀነች ያለችው ወታደራዊ መፍትሄ ላይ እንዲያተኩሩ ነው።

ይልቁንም የቡድን 7 ሀገራቱም ሆኑ ሌሎቹ ሀገራት ወደ ሰላም መንገድ በሚወስድ ተግባራዊ እርምጃ ላይ ቢያተኩሩ ሊሁሉም እንደሚያዋጣ ተመራማሪው መክረዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.