Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለታዳጊ ሃገራት ለኮቪድ19 ክትባት የሚውል 12 ቢሊየን ዶላር አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ባንክ ለታዳጊ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት የሚውል 12 ቢሊየን ዶላር አጸደቀ፡፡

ባንኩ ሃገራቱን በፋይናንስ የደገፈው ክትባቱ ዝግጁ በሚሆንበት ወቅት እንዲገዙበት እና እንዲያሰራጩበት እንዲሁም ለዜጎቻቸው ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና ክትትል እንዲያውሉት ነው ተብሏል፡፡

አሁን ይፋ ያደረገው ድጋፍ ባንኩ እስከ 2021 ድረስ ለታዳጊ ሃገራት ለመስጠት ቃል ከገባው 160 ቢሊየን ዶላር ውስጥ የሚካተት መሆኑንም በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ድጋፉ በደሃ ሃገራት የሚኖሩ ዜጎች የክትባቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ድጋፉ ሃገራቱ ፍትሐዊ የሆነ የክትባት ተደራሽነት እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ባንኩ ኢኮኖሚያቸው የተጎዳ የግል ዘርፎችን ጨምሮ በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት ተፅዕኖ ላረፈባቸው ታዳጊ ሃገራት ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ከዚህ ቀደም መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.