Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ በኬንያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል የ50 ሚሊዮን ዶላር  ብድር ፈቀደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2012(ኤፍ ቢ.ሲ) የዓለም ባንክ  በኬንያ  የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል  የሚውል የ50 ሚሊዮን ዶላር  ብድር መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡

ብድሩ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር  ለሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ  መሆኑን ነው የተነገረው፡፡

የኬንያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታሂ ካጋዌ÷ ገንዘቡ ለጤና ባለሙያዎች የመከላከያ መሳሪያዎች ግብዓት ለማሟላትና እና በሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙ የአልጋ ቁጥሮችን ለመጨመር ይውላል ነው ያሉት፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ወረርሽኙን ተከትሎ በሆስፒታሎች ውስጥ  የመከላከያ መሳሪያ እጥረት መኖሩን ቅሬታ ማሰማታቸውን  መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በዚህም የጤና ባለሙያዎች ማህበር አመራሮች  ÷ ለጤና ባለሙያዎች መንግስት አስፈላጊውን ግብዓት በማስገባት የአገር ውስጥ ምርት እንዲጨምር ና የመከላከያ መሳሪያዎች እንዲሟሉላቸው ጠይቀዋል ፡፡

አንድ የህክምና ባለሙያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ግለሰብ ጋር በነበረው ንክኪ  ምርመራ ተደርጎለት በኮሮና ቫይረስ መያዙን ተነግሯል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.