Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ30 የአፍሪካ ሃገራት ለኮቪድ19 ክትባት የሚውል ድጋፍ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ30 የአፍሪካ ሃገራት ለኮቪድ19 ክትባት የሚውል የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሚደረገው ድጋፍ በአህጉሪቷ ለወረርሽኙ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ለመከተብ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

እስካሁን ከአህጉሪቷ ውስጥ ጥቂት ሃገራት ለዜጎቻቸው ክትባት አቅርበዋል፡፡

እንዲሁም በዓለም ጤና ድርጅት ውስጥ የሚገኘው የኮቫክስ ጥምረት ለጥቂት ሃገራት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ክትባቱን እያደረሰ ይገኛል፡፡

የባንኩ ቃልአቀባይ የገንዘብ ድጋፉ ይፋ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ገንዘቡ በድጋፍ ወይም በአነስተኛ ወለድ በረዥም ጊዜ በሚከፈል ብድር መልክ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በአህጉሪቷ እስካሁን 100 ሺህ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ሲያጡ ሁለተኛው ዙር የቫይረሱ ስርጭት አድማሱን እያሰፋ እንደሚገኝ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.