Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የለውም- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት እንደሌለው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፥ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተርን የስነ ምግባር ጥሰት በተመለከተ ቦርዱ እንዲመረምር በይፋ ቅሬታ ማቅረቧን አስታውሷል።

ምንም እንኳ ቀደም ሲል የአፍሪካ እና ሌሎች ወዳጅ ሀገራትን በማስተባበር ዋና ዳይሬክተሩን እጩ አድርጋ በማቅረብ ብታስመርጣቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በህወሓት ጦርነት ሲከፈት ግን የግለሰቡ ትክክለኛ ማንነት መገለጡንና ከሀገራቸው ይልቅ የሽብር ቡድኑን መምረጣቸውን አመልክቷል ።

የተመረጡበትን ሀላፊነት የቡድኑን ፕሮፓጋንዳ ለማሠራጨት እንደተጠቀሙበት ነው መግለጫው ያብራራው።

ይህን ከድርጅቱ የስምግባር መርህ ጋር የሚጣረስ ድርጊትን ስራ አስፈፃሚ ቦርዱ እንዲመረምር በይፋ ብታመለክትም ቦርድ ጥያቄውን ተቀብሎ ከመመልከት ይልቅ ይብስኑ የኢትዮጵያ ተወካይ ይህን ጉዳይ እንዳያብራሩ መከልከሉን ነው ያስታወቀው።

በአባል ሀገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት መፈፀሙ ተቀባይነት እንደሌለው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.