Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት ሶስተኛው የኮቪድ19 ወረርሽኝ መታየት መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴልታ ዝርያ ነው የተባለው የኮቪድ19 ቫይረስ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱ ተገለፀ፡፡

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ገለጻ ሶስተኛው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ጅማሮ እየታየ ነው፡፡

ላለፉት ተከታታይ 4 ሳምንታትም ዓለም ላይ የዴልታ ዝርያ ኮቪድ19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

አዲሱ የዴልታ ቫይረስ ዝርያም አሁን ላይ በ111 ሀገራት በአስጊ ደረጃ እየተዛመተ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

የኮቪድ 19 መከላከያ መመሪያዎችን በአግባቡ አለመተግበር፣ በሚፈለገው ፍጥነት ክትባቶች ተደራሽ አለመሆናቸው እንዲሁም ክትባቶቹ የተከሰተውን የቫይረስ ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ መሆን ለቫይረሱ መዛመት ምክንያት መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በአዲሱ ዴልታ ኮቪድ19 ቫይረስም ዓለም ላይ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ቫይረሱ በሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ኢንዶኔዥያ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑንም ድርጅቱ መግለጹን የአር ቲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.