Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናን ቫይረስ መነሻ ለማወቅ ለሚያካሂደው ተጨማሪ ጥናት ያቀረበውን ጥያቄ ቻይና ውድቅ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ 19 መነሻ ላይ በመጀመሪያ ጥናቴ አልዳሰስኳቸውም ላላቸው ጉዳዮች ቻይና መረጃዎችን እንድትሰጠውና በኮሮና ቫይረስ ላይ ለሚያካሂደው ተጨማሪ ጥናትም የተለመደ ትብብሯን እንድታሳይ ጠይቋል፡፡

የቻይና ምክትል ጤና ሚኒስትር ዜንግ ዢን በበኩላቸው ÷ የዓለም ጤና ድርጅት የቻይናን የላቦራቶሪ ፕሮቶኮል ጥሶ ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ መነሻ ላይ ምርምርና በሳይንስ ተቋሞቻችን ላይ ፍተሻ ላድርግ ማለቱ እንዳስደነቃቸው ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም ÷ ቀደም ሲል አስፈላጊውን ትብብር ስናደርግ ብንቆይም ድርጅቱ ለሳይንስ ክብር የሚነፍግ፣ አቀራረቡም ትምክህት የተቀላቀለበት እና ፖለቲካዊ አዝማሚያ የተንፀባረቀበት በመሆኑ ቻይና ጥያቄውን እንደማትቀበለው መግለፃቸውን የሀገሪቱን ጤና ሚኒስቴር ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ዜንግ ÷ ቻይና ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መነሻ ላይ ጥናት እንዳደረገችና ምክረ-ሃሳቧንም ለድርጅቱ እንዳቀረበችም ጠቁመዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ ዓመት ጥር ወር ላይ የጥናት ቡድኑን ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከስቶበታል ወደ ተባለው  ዉሃን ከተማ እንደላከና ቫይረሱ ከላቦራቶሪ እንዳፈተለከ የሚያመላክት መረጃ እንዳላገኘ በጥናት ግኝቱ ማመላከቱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.