Fana: At a Speed of Life!

የዩክሬን ወታደሮች ስትራቴጂያዊ የሆነችውን ሲቪሮዶኔትስክ ከተማን ለሩሲያ ወታደሮች ትተው እየሸሹ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ሰፊ ጥቃት ሲፈፀምባት የነበረችውን ስትራቴጂያዊ ከተማ ሲቪሮዶኔትስክን ለቀው እየሸሹ ነው፡፡

የዩክሬን ወታደሮች ለሳምንታት ከዘለቀው ከባድ ጦርነት በኋላ ከተማዋን እየለቀቁ ሲሆን÷ ይህ ሩሲያ ሰፊውን የዩክሬን ምስራቃዊ ግዛት እንድትይዝ መንገድ ከፋች ነው ተብሏል።

122ኛ ቀኑን በያዘው የሩሲያ-ዩክሬን ግጭት የዩክሬን ወታደሮች በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሩሲያ ወታደሮች ከተከበበችው ሲቪሮዶኔትስክ እየለቀቁ ያሉት በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ጠንካራ ይዞታ ላይ ለመቆየት መሆኑን የዩክሬን ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡

የሉሃንስክ ክልል የአስተዳደር ማዕከል ከሆነችው  ከተማ አብዛኛው ኢንዱስትሪዎች በሩሲያ ጥቃት መውደማቸውን ነው  ቲአርቲ በዘገባው ያስነበበው።

ባለፉት ጥቂት ቀናት የሩሲያ ጦር  ሲቪሮዶኔትስክ ከተማ ዙሪያና አቅራቢያዋ በሚገኙ አካባቢዎች በዩክሬን ጦር  ላይ ባደረጉት ዘመቻ ድል ማድረጋቸውን ዘገባው ያመለከተው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.