Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ለሶማሌ ክልል የ15 ሚሊየን ብር እና የ5 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ለሶማሌ ክልል የ15 ሚሊየን ብር እና የ5 ሚሊየን ብር የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
የደቡብ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ÷ ድጋፉ ድርቁ ከእንስሳት አልፎ ሰውንም እየጎዳ በመሆኑን እና በሀሳብም በተግባርም አለን ባይነትን ለማሳየት የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉ የመጀመሪያ ዙር መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፌ ሙሃመድ በበኩላቸው፥ የተደረገው ድጋፍ ለወቅታዊ ችግር መፍቻ ከመሆን ባሻገር የደቡብ ክልል ለሶማሌ ክልል ህዝቦች ያለውን ፍቅርና ከጎን መቆምን ያሳየበት ነው ብለዋል፡፡
የገጠመው የድርቅ አደጋ ሰፊና ከባድ በመሆኑም መደጋገፍን ይጠይቃል ብለዋል።
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ የተመራው ልኡክ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ጂግጂጋ መግባቱ ይታወቃል፡፡
በጌታሰው የሸዋስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.