Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 213ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢንቨስትመንትና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ ከክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የቀረበለትን የከተማ ኢንቨስትመንት መሬት በምደባ ስለሚሰጥበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡

የገጠር ኢንቨስትመንት መሬት ለባለሀብቶች በሚተላለፍበት ሂደት እንዲሁም በአሰራሮች ላይ የተስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት በቀረበለት ምክረ ሀሳብ መመሪያ ላይ በመወያየት ሀሳብና አስተያየት በማከል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ምክር ቤቱ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን አስመልክቶ በቀረበው አጀንዳ ላይ በስፋት መክሯል፡፡

በግብርና፣ በኢንዱስትሪ ፣በአገልግሎት እና መሰል ዘርፎች ላይ የቀረቡ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለአካባቢዉ ህብረተሰብ የሚኖረዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚየዊ ፋይዳ እንዲሁም ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ሊያበረክት የሚችለዉን አስተዋፆ በመመርመር ነው ውሳኔ ያስተላለፈው፡፡

በመጨረሻም መስተዳድር ምክር ቤቱ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የቀረበለትን የአሰራር ማሻሻያዎች ላይ ተወያይቶ ሀሳብና አስተያየት በማከል የዉሳኔ ሀሳቡን ማሳለፉን ከክልሉ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.