Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት 38 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የክልሉ መንግስት በጀትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት 38 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የክልሉ መንግስት በጀትን አጽድቋል።

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው ውሎውም የ2013 የየደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት በጀትን ተመልክቷል።

ምክር ቤቱ ለ2013 በጀት ዓመት 38 ቢሊየን 21 ሚሊየን 970 ሺህ 828 ብር ሆኖ የቀረበለት የክልሉ መንግስት በጀት ላይም ተወያይቷል።

በጀቱ ከፌደራል መንግስት ድጎማ፣ ከውስጥ ገቢና ከሌሎች የገቢ አማራጮች የሚገኝ እንደሆነ በጉባኤው ላይ መነሳቱን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 28 ቢሊየን ከፌደራል መንግስት የሚገኝ ድጎማ ሲሆን፥ 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚሆነው ደግሞ ከክልሉ ልዩ ልዩ ገቢዎች የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት ዓምናው ማለትም ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃር የ12 ነጥብ 24 በመቶ ብልጫ ያመው መሆኑም ተጠቁሟል።

የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በበጀቱ ላይ በሰጡት ማብራሪያም፥ በ2013 በጀት በሁሉም ዘርፎች የበጀት አቅምን ባገናዘበ መልኩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የበጀት ክፍተት ከተገኘ ደግሞ አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች በጥናት ላይ በመመርኮዝ እንደሚሰራም ነው አቶ ርስቱ ያብራሩት።

የክልሉ ምክር ቤትም በቀረበለት የ2013 የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምጽና በአንድ ድምፀ ታቅቦ አጽድቆታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.