Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ሰመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ፣የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አፋር ክልል ሰመራ ገብተዋል፡፡

የደቡብ ክልል አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ በማለም ነው ዛሬ በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልኡክ ወደ ሰመራ ያቀናው ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ለተመራው ልኡካን ቡድን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል ማድረጋቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ትላንት የደቡብ ክልል በአማራ ክልል በአሸባሪው ትህነግ ለተፈናቀሉ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.