Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ከሰሜን ኮሪያ ጋር ሠላም ለማስፈን እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን፥  ከሰሜን ኮሪያ ጋር “የማይቀለበስ የሠላም መንገድ” ብለው የገለጹትን ግንኙነት ለመመስረት ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ፥ ደቡብ ኮሪያ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ እና የማይቀለበስ የሠላም አማራጭ ለመከተል እንደሚሰሩም ነው ቃል የገቡት፡፡

ደቡብ ኮሪያ፥ በኮሪያ ልሣነ-ምድር ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከፈረንጆቹ 1950 እስከ 53 ጥረት ብታደርግም ከሰሜን ኮሪያ በኩል ግን “በመጀመሪያ አሜሪካ በውስጥ ጉዳዬ ላይ ያላትን አቋም ታስተካክል”  በሚል ሰበብ ለሠላሙ ጥሪ ኦፊሴላዊ ምላሽ ሳትቸረው ቆይታለች፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ለሰሜን ኮሪያ ምንም አይነት ጥላቻ የለኝም፤ በማናቸው ጉዳዮችም ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ስትል ማስታወቋን ዘ ኢፖክ ታይምስ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.