Fana: At a Speed of Life!

የደብረታቦርና ወልዲያ ከተሞች ወደ ሪጆፖሊታንት ደረጃ እንዲያድጉ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የደብረታቦርና ወልዲያ ከተሞች ወደ ሪጆፖሊታንት ደረጃ እንዲያድጉ ወሰነ።

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው የ6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ የደብረታቦርና ወልዲያ ከተሞች ወደ ሪጆፖሊታንት ከተማነት ለማደግ ያቀረቡትን ጥያቄ መርምሮ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ከተሞቹ ወደ እዚህ ደረጃ ለማደግ የተቀመጡ መስፈርቶችን ስለማሟላታቸው በጥናት ተደግፎ የቀረበለትን ሰነድ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ ነው።

ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ለደብረብርሃን፣ ደብረ ማርቆስና ኮምቦልቻ ከተሞችም ወደ ጆፖሊታንት ደረጃ እንዲያድጉ መወሰኑም ይታወሳል።

ምክር ቤቱ በዕለቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መክሮም ውሳኔዎችን ማሳለፉን ከክልሉ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል በተለያዬ ደረጃ የሚጠሩ 660 ከተሞች እንዳሉና ከክልሉ ህዝብ 22 በመቶ የሚሆነው የከተማ ነዋሪ እንደሆነ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.