Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ሆላንድ የዶሮ እርባታ ድርጅት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዶሮ እርባታ እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን አካባቢ የሚገኘው የደብረ ሆላንድ የዶሮ እርባታ ድርጅት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዶሮ ማርባት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ከሁለት አመት በፊት በዘርፉ የተሰማራው ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከ40 ሺህ በላይ የዶሮ ጫጩቶችን እየተንከባከበ እንደሚገኝ የድርጅቱ ተወካይ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት አለምፀሀይ እስጢፋኖስ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ከእንቁላል ጣይ ዶሮዎች በየቀኑ ከ30 ሺህ በላይ እንቁላሎችን እየሰበሰበ መሆኑን ጠቅሰው፥ የወረዳው አስተዳደር ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

ከ20 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠርም ለአካባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማትን በመገንባትና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 51 ነዋሪዎች የጤና መድህን ሽፋን ክፍያ መፈጸሙንም ገልጸዋል።

በሰላም አሰፋ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.