Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ማርቆስ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃን ለማሻሻል ከ260 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ማርቆስ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃን ለማሻሻል ከ260 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታ ተጀመረ።

የደብረ ማርቆስ ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

በተመሳሳይ ለስናን ወረዳ ርዕሰ ከተማ ረዕቡ ገበያ ከተማ በ 123 ሚሊየን ብር ወጪየሚካሄድ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የአብክመ የውሀ ሀብት ልማት እና ኢነርጅ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው ፣ የአብክመ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ጥላሁን መሀሪ ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሀም አያሌው እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.