Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራው ማህበረሰብ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዳያስፖራው ማህበረሰብ ግዙፉን የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ።
ዳያስፖራዎቹ ሰሞኑን በሲዳማ ክልል ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ሲጎበኙ የቆዩ ሲሆን፥ ዛሬ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመጎብኘት ያሉ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተመልክተዋል።
በጉብኝት መርሀ ግብሩ ላይ ከ150 በላይ የሚሆኑ ዳያስፖራዎች የተገኙ ሲሆን፥ በፋብሪካዎች ውስጥ ያሉ የምርት ሂደቶችን፣ የፓርኩን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁን ላይ በፓርኩ የሚገኙ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችን ጎብኝተዋል።
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ፥ ለዳያስፖራው በፓርኩ ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን እንቅስቃሴዎቹንም ለዳያስፖራው አስጎብኝተዋል።
ዳያስፖራው ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመጠቀም መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስና ክልሉን ብሎም ኢትዮጵያን በኢኮኖሚው ዘርፍ እንዲደግፍ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑ ዳያስፖራዎች በጉብኝቱ ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀው፥ በፓርኩ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ ፍቃደኞች መሆናቸውን አሳውቀዋል።
እስካሁን ድረስ የዳያስፖራው ማህበረሰብ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ የሚያስተዳድራቸውን አምስት ፓርኮች መጎብኘት መቻሉን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.