Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራ አገልግሎት በግጭት ምክንያት የተጎዱ ተቋማትን እንደሚገነባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራ አገልግሎት በግጭት ምክንያት የተጎዱ ተቋማትን መገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከጤና እና ትምህርት ሚኒስቴሮች ጋር ተፈራርሟል፡፡
አገልግሎቱ በግጭት ምክንያት የተጎዱ ተቋማትን የሚገነባው ከዳያስፖራው በሚሰበሰብ ሀብት መሆኑን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ እንደገለጹት÷ ከዳያስፖራው የሚሰበሰበውን ሀብት ለማሳደግና በዕቅድ ለተያዙ ፕሮጀክቶች ለማዋል መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡
ሚኒስቴሮቹ በግጭት ምክንያት የተጎዱ ተቀማትን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ዳያስፖራው የተለመደ ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ድጋፉ “አይዞን ኢትዮጵያ”ን ጨምሮ በተለያዩ አግባቦች እንደሚሰባሰብ ጠቁመው÷ የሚሰባሰበውን ሀብት ሁለቱ ተቋማት የሚያስተዳድሩትና በአፈጻጸሙም ላይ ጠንካራ ክትትል የሚደረግበት ይሆናል ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ በግጭቱ ምክንያት ከአራት ሺህ በላይ የትምህርት ተቋማት መጎዳታቸውን አስታውሰው÷ ከደረሰው ጉዳት አንጻር ለሥራው ከፍተኛ ሀብት ማሰባሰብ ይገባል ብለዋል፡፡
ለዚህም ከዳያስፖራው ሀብት በማሰባሰብም ሆነ የዕውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር በማረጋገጥ የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ በኩል ብዙ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ በግጭቱ ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁመው÷ ከዳያስፖራውና ከሌሎች አካላት በተገኘ ድጋፍ የተወሰኑ የጤና ተቋማት ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ከጉዳቱ ስፋት አንጻር ዘርፉ የዳያስፖራውንም ሆነ የሌሎች በጎ አድራጊ ተቋማትን ድጋፍ እንደሚፈልግ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.