Fana: At a Speed of Life!

የድምፀ ወያኔ (DW international )የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኞች ህዝብን ይቅርታ ጠየቁ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የድምፀ ወያኔ (DW international )የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኞች ህዝብን ይቅርታ መጠየቃቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የጁንታው ቡድን ልሳን የነበረው ድምፀ ወያኔ በቴሌቪዥን ጣቢያው ከወራት በፊት በኦሮሚኛ ቋንቋ ስርጭት በመጀመር የውሸት ዘገባዎችንና በጋዜጠኞች መርሆ ፀያፍ የሆኑ በሀገር ህልውና ላይ ጫና የሚፈጥሩ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷል ።
በኦሮምኛ ቋንቋ ሲሰሩ ከነበሩ 4 ጋዜጠኞች ውስጥ ሶስቱ ግርማ ጉዲሳ ፣ ካሊድ አድቡልፈታ እና ሙስጠፋ ቃሊዩ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በፍቃዳቸው በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሚዲያ እና ወንጀል ምርመራ ቢሮ የነበረውን ነገር አስረድተዋል ብሏል ኮሚሽኑ ።
ጋዜጠኞቹ እንዳስረዱትም የቅጥር ማስታወቂው የወጣው በትግራይ ቲቪ በኦሮምኛ ቋንቋ ስርጭት ስለሚጀምር በሚል ሲሆን በፈተናው ወቅትም የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦቸ ገፅታ የሚገነቡ ዝግጅቶች ላይ ያተኮረ ስራ እንደምንሰራ ነበር የተነገረን ብለዋል።
ወደ መቐለ ከተጓዝን በኋላ ግን ድምጸ ወያኔ ተመድበን ብሄር ብሄረሰብን በመንግስት ላይ ማሳመፅ እና የእርስ በእርስ ብጥብጥ መፍጠር ላይ ያተኮረ ፅሁፍ እየተሰጣቸው በግዴታ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል ።
በዘገባቸውም በኮቪድ ምክንያት የተራዘመውን ሀገራዊ ምርጫ መቃወም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰላም የኖቬል ሽልማት አግባብ አይደለም ብሎ ለማሰረዝ መጣር ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴና ተግባር ሁሉ በተቃራኒ መልኩ በመጥፎ ጎን ትንታኔ መስጠት ላይ በማተኮር በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲያቀርቡ ይገደዱ እንደነበር አስረድተዋል ።
በክልሉ በነበረው ህግም የማስከበር ዘመቻ ጣቢያው ከመቐለ ከተማ ቁሳቁሱን ጭኖ ጋዜጠኖችንም በማስገደድ ወደማያቁት ቦታ በመውሰድ በደረሱበት ሁሉ ስርጭት ለመጀመር እየተሞከረ ባለበት ወቅት ከመከላከያ ሰራዊት የሚደርስበት ጥቃት በማየሉ የጁንታው ቡድን ሲሸሽ ጋዜጠኞቹ ረጅም የእግር ጉዞ በማድረግ እና መቐለ በመግባት በፍቃዳው ይህንን መረጃ ሰጥተዋል ብሏል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ።
ጋዜጠኞቹም ለቡድኑ ጋር በመሆን ለሰራነው መጥፎ ስራ ህዝብ ይቅርታ ያድርግል ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.