Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት የተጀመረው የድሬዳዋ ምክር ቤት ጉባዔ ለሥራ ዘመኑ ማስፈጸሚያ ከ4 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት እንዲሁም የዳኛ ሹመትና አዋጅ በማጽደቅ ዛሬ ተጠናቋል።
ምክር ቤቱ ያጸደቀው በጀት የሕዝብ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚያግዙ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በጀቱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ750 ሚሊየን ብር ጭማሪ እንዳለው የአስተዳደሩ ኢኮኖሚና ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልዩ ተናግረዋል፡፡
ከበጀቱ ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በሚያግዙ ነባር ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.