Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ፖሊስ የደንብ ልብሱን ቀየረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ፖሊስ አዲሱን የፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ በዛሬው ዕለት በይፋ  አስመርቋል፡፡
 
የደንብ ልብሱ አሁን ላይ የተቋሙን ቁመና በሚገልጽ መልኩ እና አዲሱ የተቋሙ አርማ ያረፈበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በተጨማሪም አዲሱ የደንብ ልብስ በፊት አባላት ያነሷቸው የነበሩ የጥራትና ተያያዥ ችግሮችን የፈታ መሆኑን ከድሬ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በደንብ ልብስ ምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ፣ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሰራዊቱ አባላት ተገኝተዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ኢትዮጵያ
 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.