Fana: At a Speed of Life!

የጀርመን ቡንደስሊጋ ግንቦት 1 ወደ ውድድር ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን የሀገሪቱ እግር ኳስ ሊግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለማችን ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በርካታ ታላላቅ የሊግ ውድድሮች መቋረጣቸው ይታወቃል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከተቋረጡ የሊግ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀርመን ቡንደስሊጋ በቅርቡ ወደ ውድድር ለመመለስ ፍላጎት እንዳለው የጀርመን እግር ኳስ ሊግ አስታውቋል።

ቡንደስሊጋው የፊታችን ግንቦት 1 ወደ ውድድር በመመለስ ያለ ተመልካች ውድድሮቹን አድርጎ ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆኑን የእግር ኳስ ሊጉ ገልጿል።

ቡንደስሊጋውን እና የሁለተኛ ዲቪዥን ጨዋታዎችን የሚያስተዳደረው የጀርመን እግር ኳስ ሊግ በዛሬው እለት ከ36 ፕሮፌሽናል ክለቦች ጋር ከተወያየ በኋላ ነው የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ያለተመልካች የመጨረስ ፍላጎት እንዳለው የገለፀው።

ሆኖም ግን በሀገሪቱ የሰዎች እንቅስቃሴ በተገደደበት በዚህ ወቅት የጀርመን እግር ኳስ ሊግ አስተዳዳሪዎች ፍቃድ ያገኛሉ የሚለው ጥያቄ ሆኗል።

የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክርስቲያን ሲፈርት “ግንቦት ወር ውድድር ለመጀመር ዘግጅ ነን፤ የሚራዘም ከሆነም ለዚያም እንዘጋጃለን” ብለዋል።

የጀርመን መንግስት የኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር በሚል ብዙ ሰው የሚሰበሰብበት ሁነት እስከ ነሀሴ ወር መጨራሻ እንደማይኖር ማስታወቁ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.